የዳዊት መዝሙር።
1ለእግዚአብሔር ዐዲስ ምስጋናን አመስግኑ እግዚአብሔር ተኣምራትን አድርጓልና ቀኙ የተቀደሰም ክንዱ ለርሱ ማዳን አደረገ 2እግዚአብሔር ማዳኑን አስታወቀ በአሕዛብም ፊት ጽድቁን ገለጠ 3ለያዕቆብ ምሕረቱን ለእስራኤልም ቤት እውነቱን ዐሰበ የምድር ዳርቻዎች ዅሉ የአምላካችንን ማዳን አዩ 4ምድር ዅሉ ሆይ ለእግዚአብሔር እልል በሉ አመስግኑ ደስ ይበላችኹ ዘምሩም 5ለእግዚአብሔር በመሰንቆ በመሰንቆና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩ 6በዋሽንትና በመለከት ድምፅ በንጉሥ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ 7ባሕርና ሞላዋ ዓለምም በርሷም የሚኖሩ ይናወጡ 8ወንዞችም በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ ተራራዎች ደስ ይበላቸው በምድር ሊፈርድ ይመጣልና 9ለዓለምም በጽድቅ ለአሕዛብም በቅንነት ይፈርዳል