የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር ነገሠ አሕዛብ ይደንግጡ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ ምድር ትናወጥ 2እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው ርሱም በአሕዛብ ዅሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ 3ግሩምና ቅዱስ ነውና ዅሉ ታላቅ ስምኽን ያመስግኑ 4የንጉሥ ክብር ፍርድን ይወዳ፟ል አንተ ቅንነትን አጸናኽ ለያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ አደረግ ኽ 5አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት ቅዱስ ነውና ወደእግሩ መረገጫ ስገዱ 6ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው እግዚአብሔርን ጠሩት ርሱም መ ለሰላቸው 7በደመና ዐምድም ተናገራቸው ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ 8አቤቱ አምላክችን ሆይ አንተ ሰማኻቸው አቤቱ አንተ ማርኻቸው ሥራቸውን ዅሉ ግን ተበቀልኻቸው 9አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት በቅዱስ ተራራውም ስገዱ አምላካችን እግዚአብሔር ቅ ዱስ ነውና