የዳዊት ምስጋና መዝሙር።
1ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን ለአምላክ ለመድኀኒታችን እልል እንበል 2በምስጋና ወደ ፊቱ እንድረስ በዝማሬም ለርሱ እልል እንበል 3እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና በአማልክትም ዅሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነውና 4እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥላቸውም የምድር ዳርቻዎችም በእጁ ውስጥ ናቸው የተራራዎች ከፍታዎች የር ሱ ናቸው 5ባሕር የርሱ ናት ርሱም አደረጋት የብስንም እጆቹ ሠሯት 6ኑ እንስገድ ለርሱም እንገዛ በርሱ ባደረገን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ 7ርሱ አምላካችን ነውና እኛ የማሰማሪያው ሕዝብ የእጁም በጎች ነንና 8በምድረ በዳ እንደ ተፈታተኑት እንዳስቈጡት ጊዜ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ ልባችኹን አታጽኑ 9የተፈታተኑኝ አባቶቻችኹ ፈተኑኝ ሥራዬንም አዩ 10ያችን ትውልድ አርባ ዓመት ተቈጥቻት ነበር ዅልጊዜ ልባቸው ይስታል እነርሱም መንገዴን አላወቁም አልኹ 11ወደ ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቍጣዬ ማልኹ