በአራተኛ ሰንበት የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር የበቀል አምላክ ነው የበቀል አምላክ ተገለጠ 2የምድር ፈራጅ ሆይ ከፍ ከፍ በል ለትዕቢተኛዎች ፍዳቸውን ክፈላቸው 3አቤቱ ኀጢአተኛዎች እስከ መቼ ኀጢአተኛዎች እስከ መቼ ይጓደዳሉ 4ይከራከራሉ ዐመፃንም ይናገራሉ ዐመፃንም የሚያደርጉ ዅሉ ይናገራሉ 5አቤቱ ሕዝብን አዋረዱ ርስትኽንም አስቸገሩ 6ባልቴቲቱንና ድኻ አደጉን ገደሉ ስደተኛውንም ገደሉ 7እግዚአብሔር አያይም የያዕቆብ አምላክ አያስተውልም አሉ 8የሕዝብ ደንቈሮዎች ሆይ አስተውሉ ሰነፎችማ መቼ ይጠበባሉ 9ዦሮን የተከለው አይሰማምን ዐይንን የሠራው አያይምን 10አሕዛብንስ የሚገሥጸው ለሰውም ዕውቀት የሚያስተምረው ርሱ አይዘልፍምን 11የሰዎች ዐሳብ ከንቱ እንደ ኾነ እግዚአብሔር ያውቃል 12-13 ለኀጢአተኛ ጕድጓድ እስኪቈፈር ድረስ ከክፉዎች ዘመናት ይወገድ ዘንድ አቤቱ አንተ የገሠጽኸው ሕግኽንም ያስተማርኸው ሰው ምስጉን ነው 14እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥልምና ርስቱንም አይተውምና 15ፍርድ ወደ ጽድቅ እስኪመልስ ድረስ ልበ ቅኖችም ዅሉ ይከተሏታል 16በክፉዎች ላይ ለእኔ የሚቆም ማን ነው ዐመፃንስ በሚያደርጉ ላይ ለእኔ የሚከራከር ማን ነው 17እግዚአብሔር የረዳኝ ባይኾን ነፍሴ ለጥቂት ጊዜ በሲኦል ባደረች ነበር 18እግሮቼ ተሰናከሉ ባልኹ ጊዜ አቤቱ ምሕረትኽ ረዳኝ 19አቤቱ ለልቤ እንደ መከራዋ ብዛት ማጽናናትኽ ነፍሴን ደስ አሠኛት 20በሕግ ላይ ዐመፅን የሚሠራ የዐመፅ ዙፋን ከአንተ ጋራ አንድ ይኾናልን 21የጻድቅን ነፍስ ያደቡባታል በንጹሕ ደምም ይፈርዳሉ 22እግዚአብሔር መጠጊያ ኾነኝ አምላኬ የተስፋዬም ረዳት ነው 23እንደ በደላቸውም እንደ ክፋታቸውም ፍዳቸውን ይከፍላቸዋል አምላካችን እግዚአብሔርም ያጠፋቸዋል