በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር።
1እግዚአብሔር ነገሠ ክብርንም ለበሰ እግዚአብሔር ኀይልን ለበሰ ታጠቀም ዓለምን እንዳትናወጥ አጸና ት 2ዙፋንኽ ከጥንት ዠምሮ የተዘጋጀ ነው አንተም ከዘለዓለም ነኽ 3አቤቱ ወንዞች ከፍ ከፍ አደረጉ ወንዞች ቃሎቻቸውን ከፍ ከፍ አደረጉ 4ከብዙ ውሃዎች ድምፅ ከባሕርም ታላቅ ሞገድ ይልቅ እግዚአብሔር በከፍታው ድንቅ ነው 5ምስክርኽ እጅግ የታመነ ነው አቤቱ እስከ ረዥም ዘመን ድረስ ለቤትኽ ቅድስና ይገ፟ባ፟ል