ለመዘምራን አለቃ በሙት ላቤን የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ በልቤ ዅሉ አመሰግንኻለኹ ተኣምራትኽንም ዅሉ እነግራለኹ 2ባንተ ደስ ይለኛል ሐሤትንም አደርጋለኹ ልዑል ሆይ ለስምኽ እዘምራለኹ 3ጠላቶቼ ወደ ዃላ በተመለሱ ጊዜ ይሰናከላሉ ከፊትኽም ይጠፋሉ 4ፍርዴንና በቀሌን አድርገኽልኛልና ጽድቅን እየፈረድኽ በዙፋንኽ ላይ ተቀመጥኽ 5አሕዛብን ገሠጽኽ ዝንጉዎችንም አጠፋኽ ስማቸውንም ለዘለዓለም ደመሰስኽ 6ጠላቶች በጦር ለዘለዓለም ጠፉ ከተማዎቻቸውንም አፈረስኽ ዝክራቸውም በአንድነት ጠፋ 7እግዚአብሔር ግን ለዘለዓለም ይኖራል ዙፋኑንም ለመፍረድ አዘጋጀ 8ርሱም ዓለምን በጽድቅ ይፈርዳታል አሕዛብንም በቅንነት ይዳኛቸዋል 9እግዚአብሔርም ለድኻዎች መጠጊያ ኾናቸው ርሱም በመከራቸው ጊዜ ረዳታቸው ነው 10ስምኽን የሚያውቁ ዅሉ ባንተ ይታመናሉ አቤቱ የሚሹኽን አትተዋቸውምና 11በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ በአሕዛብም መካከል አደራረጉን ንገሩ 12ደማቸውን የሚመራመር ርሱ ዐስቧልና የድኻዎችንም ጩኸት አልረሳምና 13አቤቱ ዕዘንልኝ ጠላቶቼም የሚያመጡብኝን መከራ እይ ከሞት ደጆች ከፍ ከፍ የምታደርገኝ 14ምስጋናውን ዅሉ እናገር ዘንድ በጽዮን ልጅ በደጆቿ በማዳንኽ ደስ ይለኛል 15አሕዛብ በሠሩት ጕድጓድ ወደቁ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች 16እግዚአብሔር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው ኀጢአተኛው በእጆቹ ሥራ ተጠመደ 17ኀጢአተኛዎች ወደ ሲኦል ይመለሳሉ እግዚአብሔርን የሚረሱ አሕዛብም ዅሉ 18ድኻ ለዘለዓለም አይረሳምና የችግረኛዎችም ተስፋቸው ለዘለዓለም አይጠፋም 19አቤቱ ተነሥ ሰውም አይበርታ አሕዛብም በፊትኽ ይፈረድባቸው 20አቤቱ ፍርሀትን በላያቸው ጫንባቸው አሕዛብ ሰዎች እንደ ኾኑ ይወቁ (መዝሙረ 10 በዕብራይስጥ) 1አቤቱ ለምን ርቀኽ ቆምኽ በመከራም ጊዜ ለምን ትሰወራለኽ 2በኀጢአተኛ ትዕቢት ድኻ ይናደዳል ባሰቡት ተንኰላቸው ተጠመዱ 3ኀጢአተኛ በነፍሱ ፈቃድ ይወደሳልና ዐመፀኛም ይባርካል 4ኀጢአተኛ እግዚአብሔርን አበሳጨው እንደ ቍጣውም ብዛት አይመራመረውም በርሱ ፊት እግዚአብሔር የለ ም 5መንገዱ ዅሉ የረከሰ ነው ፍርድኽም በፊቱ የፈረሰ ነው ጠላቶችንም ዅሉ ይገዛቸዋል 6በልቡ ይላል፦ለልጅ ልጅ አልታወክም ክፉም አያገኘኝም 7አፉ መርገምንና ሽንገላን ተንኰልን የተመላ ነው ከምላሱ በታች ጕዳትና መከራ ነው 8በመንደሮች መሸመቂያ ይቀመጣል ንጹሓንን በስውር ይገድል ዘንድ ዐይኖቹም ወደ ድኻ ይመለከታሉ 9እንደ አንበሳ በችፍግ ዱር በስውር ይሸምቃል ድኻውን ለመንጠቅ ያደባል ድኻውን ይነጥቀዋል በአሽክ ላውም ይስበዋል 10ድኻ ይዋረዳል ይጐብጣል በኀያላኑም እጅግ ይወድቃል 11በልቡም ይላል፦እግዚአብሔር ረስቶኛል ፈጽሞም እንዳያይ ፊቱን ሰወረ 12አቤቱ አምላክ ሆይ ተነሥ እጅኽም ከፍ ከፍ ትበል ድኻዎችን አትርሳ 13ኀጢአተኛ ስለ ምን እግዚአብሔርን አስቈጣው በልቡ፦አይመራመረኝም ይላልና 14አየኸው አንተ ክፋትንና ቍጣን ትመለከታለኽና በእጅኽ ፍዳውን ለመስጠት ድኻ ራሱን ለአንተ ይተዋ ል ለድኻ አደግም ረዳቱ አንተ ነኽ 15የኀጢአተኛንና የክፉን ክንድ ስበር የኀጢአቱንም ብድራት ክፈል ሌላ እስከማይገኝ ድረስ 16እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይነግሣል አሕዛብ ከምድሩ ይጠፋሉ 17እግዚአብሔር የድኻዎችን ምኞት ሰማ ዦሮውም የልባቸውን ዐሳብ አደመጠች 18ፍርዱ ለድኻ አደግና ለችግረኛ ይደረግ ዘንድ ሰዎች በምድር ላይ አፋቸውን ከፍ ከፍ ማድረግ እን ዳይደግሙ