ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ ጌታችን ስምኽ በምድር ዅሉ እጅግ ተመሰገነ ምስጋናኽ በሰማዮች ላይ ከፍ ከፍ ብሏልና 2ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀኽ ስለ ጠላትኽ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት 3የጣቶችኽን ሥራ ሰማዮችን ባየኹ ጊዜ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራኻቸውን 4ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው 5ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው 6በእጆችኽም ሥራ ዅሉ ላይ ሾምኸው ዅሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛኽለት 7በጎችንም ላሞችንም ዅሉ ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሳዎች 8የሰማይንም ወፎች የባሕርንም ዓሣዎች በባሕር መንገድ የሚኼደውንም ዅሉ፦ 9አቤቱ ጌታችን ስምኽ በምድር ዅሉ እጅግ ተመሰገነ