ስለ ብንያማዊ ሰው ስለ ኩዝ ቃል ለእግዚአብሔር የዘመረው የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ አምላኬ ባንተ ታመንኹ ከሚያሳድዱኝ ዅሉ አድነኝና አውጣኝ 2ነፍሴን እንደ አንበሳ ነጥቀው እንዳይሰብሯት የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር 3አቤቱ አምላኬ እንዲህስ ካደረግኹ ዐመፃም በእጄ ቢኖር 4ክፉ ላደረጉብኝም ክፉን መልሼላቸው ብኾን ጠላቴንም በከንቱ ገፍቼው ብኾን 5ጠላት ነፍሴን ያሳዳ፟ት ያግኛትም ሕይወቴንም በምድር ላይ ይርገጣት ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርዳ ት 6አቤቱ በመዓትኽ ተነሥ በጠላቶቼ ላይ በቍጣ ተነሣባቸው አቤቱ አምላኬ ባዘዝኸው ትእዛዝ ንቃ 7የአሕዛብም ጉባኤ ይከብ፟ኻል በእነርሱም ላይ ወደ ከፍታ ተመለስ 8እግዚአብሔር በአሕዛብ ይፈርዳል አቤቱ እንደ ጽድቄ ፍረድልኝ እንደ የዋህነቴም ይኹንልኝ 9የኃጥኣን ክፋት ይጥፋ ጻድቁን ግን አቅና እግዚአብሔር ልቡናንና ኵላሊትን ይመረምራል 10እግዚአብሔር የጽድቅ ጋሻዬ ነው ልበ ቅኖችን የሚያድናቸው 11እግዚአብሔር የእውነት ዳኛ ነው ኀይለኛም ታጋሽም ነው ዅልጊዜም አይቈጣም 12ባትመለሱ ግን ሰይፉን ይስላል ቀስቱን ገተረ አዘጋጀም 13የሞት መሣሪያንም አዘጋጀበት ፍላጻዎቹንም የሚቃጠሉ አደረገ 14እንሆ በዐመፃ ተጨነቀ ጕዳትን ፀነሰ ኀጢአትንም ወለደ 15ጕድጓድን ማሰ ቈፈረም ባደረገውም ጕድጓድ ይወድቃል 16ጕዳቱ በራሱ ይመለሳል ዐመፃውም በዐናቱ ላይ ትወርዳለች 17እግዚአብሔርን እንደ ጽድቁ መጠን አመሰግናለኹ ለልዑል እግዚአብሔርም ስም እዘምራለኹ