ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች ስለ ስምንተኛ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ በቍጣኽ አትቅሠፈኝ በመዓትኽም አትገሥጸኝ 2ድውይ ነኝና አቤቱ ማረኝ ዐጥንቶቼ ታውከዋልና ፈውሰኝ 3ነፍሴም እጅግ ታወከች አንተም አቤቱ እስከ መቼ ድረስ ነው 4አቤቱ ተመለስ ነፍሴንም አድናት ስለ ቸርነትኽም አድነኝ 5በሞት የሚያስብኽ የለምና በሲኦልም የሚያመሰግንኽ ማን ነው 6በጭንቀቴ ደክሜያለኹ ሌሊቱን ዅሉ ዐልጋዬን ዐጥባለኹ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለኹ 7ዐይኔ ከቍጡ ዕንባ የተነሣ ታወከች ከጠላቶቼ ዅሉ የተነሣ አረጀኹ 8ዐመፃን የምታደርጉ ዅሉ ከእኔ ራቁ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ቃል ሰምቷልና 9እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማኝ እግዚአብሔር ጸሎቴን ተቀበለ 10ጠላቶቼ ዅሉ ይፈሩ እጅግም ይጐስቍሉ ወደ ዃላቸው ይመለሱ በፍጥነትም ይፈሩ