ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ ቃሌን አድምጥ ጩኸቴንም አስተውል 2የልመናዬን ቃል አድምጥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ አቤቱ ወዳንተ እጸልያለኹና 3በማለዳ ድምፄን ትሰማለኽ በማለዳ በፊትኽ እቆማለኹ እጠብቃለኹም 4አንተ በደልን የማትወድ፟ አምላክ ነኽና ክፉ ከአንተ ጋራ አያድርም 5በከንቱ የሚመኩ በዐይኖችኽ ፊት አይኖሩም ክፉ አድራጊዎችን ዅሉ ጠላኽ 6ሐሰትን የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለኽ ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው እግዚአብሔር ይጸየፋል 7እኔ ግን በምሕረትኽ ብዛት ወደ ቤትኽ እገባለኹ አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናኽ መቅደስ እሰግዳለ ኹ 8አቤቱ ስለ ጠላቶቼ በጽድቅኽ ምራኝ መንገዴን በፊትኽ አቅና 9በአፋቸው እውነት የለምና ልባቸውም ከንቱ ነው ጕረሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው በምላሳቸው ይሸነግ ላሉ 10አቤቱ ፍረድባቸው በምክራቸውም ይውደቁ ስለ ክፋታቸውም ብዛት አሳዳ፟ቸው እነርሱ ዐምፀውብኻልና 11ባንተ የሚታመኑት ዅሉ ግን ደስ ይላቸዋል ለዘለዓለሙ ደስ ይላቸዋል እነርሱንም ትጠብቃለኽ ስምኽ ንም የሚወዱ ዅሉ ባንተ ይመካሉ 12አንተ ጻድቁን ትባርከዋለኽና አቤቱ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸን