ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች የዳዊት መዝሙር።
1የጽድቄ አምላክ በጠራኹት ጊዜ መለሰልኝ በጭንቀቴም አሰፋኽልኝ ማረኝ ጸሎቴንም ስማ 2እናንት የሰው ልጆች እስከ መቼ ድረስ ልባችኹን ታከብዳላችኹ 3እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ ዕወቁ እግዚአብሔር ወደ ርሱ በተጣራኹ ጊዜ ይሰማኛል 4ተቈጡ ነገር ግን ኀጢአትን አታድርጉ በመኝታችኹ ሳላችኹ በልባችኹ ዐስቡ ዝም በሉ 5የጽድቅን መሥዋዕት ሠዉ በእግዚአብሔርም ታመኑ 6በጎውን ማን ያሳየናል የሚሉ ብዙ ናቸው አቤቱ የፊትኽ ብርሃን በላያችን ታወቀ 7በልቤ ደስታን ጨመርኽ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ 8በሰላም እተኛለኹ አንቀላፋለኹም አቤቱ አንተ ብቻኽን በእምነት አሳድረኸኛልና