የዳዊት መዝሙር፥ ከልጁ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸ ጊዜ።
1አቤቱ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ! በእኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው 2ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦አምላክሽ አያድንሽም አሏት 3አንተ ግን አቤቱ መጠጊያዬ ነኽ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነኽ 4በቃሌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለኹ ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል 5እኔ ተኛኹ አንቀላፋኹም እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃኹ 6ከሚከቡ፟ኝ ከአእላፍ ሕዝብ አልፈራም 7ተነሥ አቤቱ አምላኬ ሆይ አድነኝ አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተኻልና የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረኻ ልና 8ማዳን የእግዚአብሔር ነው በረከትኽም በሕዝብኽ ላይ ነው