ትንቢት ስለ ክርስቶስ
1አሕዛብ ለምን ያጕረመርማሉ ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ 2የምድር ነገሥታት ተነሡ አለቃዎችም በእግዚአብሔርና በመሲሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ 3ማሰሪያቸውን እንበጥስ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል 4በሰማይ የሚኖር ርሱ ይሥቃል ጌታም ይሣለቅባቸዋል 5በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል በመዓቱም ያውካቸዋል 6እኔ ግን ንጉሤን ሾምኹ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ 7ትእዛዙን እናገራለኹ እግዚአብሔር አለኝ፦አንተ ልጄ ነኽ እኔ ዛሬ ወለድኹኽ 8ለምነኝ አሕዛብን ለርስትኽ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትኽ እሰጥኻለኹ 9በብረት በትር ትጠብቃቸዋለኽ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለኽ 10አኹንም እናንት ነገሥታት ልብ አድርጉ እናንት የምድር ፈራጆችም ተገሠጹ 11ለእግዚአብሔር በፍርሀት ተገዙ በረዓድም ደስ ይበላችኹ 12ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ ቍጣው ፈጥና ትነዳ፟ለችና በርሱ የታመኑ ዅሉ የተመሰገኑ ናቸው