የጻድቃንና የኃጥኣን ትርጓሜ
1ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልኼደ በኀጢአተኛዎችም መንገድ ያልቆመ በዋዘኛዎችም ወንበር ያልተቀ መጠ 2ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል 3ርሱም በውሃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ ቅጠሏም እንደማይረግፍ ዛ ፍ ይኾናል የሚሠራውም ዅሉ ይከናወንለታል 4ክፉዎች እንዲህ አይደሉም ነገር ግን ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ ናቸው 5ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ ኀጢአተኛዎችም በጻድቃን ማኅበር አይቆሙም 6እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች