ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1በእግዚአብሔር ታመንኹ ነፍሴን፦እንደ ወፍ ወደ ተራራዎች ተቅበዝበዢ እንዴት ትሏታላችኹ 2ኀጢአተኛዎች እንሆ ቀስታቸውን ገትረዋልና ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና ልበ ቅኖችን በስው ር ይነድፉ ዘንድ 3አንተ የሠራኸውን እንሆ እነርሱ አፍርሰዋልና ጻድቅ ግን ምን አደረገ 4እግዚአብሔር በተቀደሰው መቅደሱ ነው እግዚአብሔር ዙፋኑ በሰማይ ነው ዐይኖቹ ወደ ድኻ ይመለከታሉ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ 5እግዚአብሔር ጻድቅንና ኀጥእን ይመረምራል ዐመፃን የወደዳት ግን ነፍሱን ጠልቷል 6ወጥመድ በኃጥኣን ላይ ያዘንባል እሳትና ዲን ዐውሎ ነፋስም የጽዋቸው ዕድል ፈንታ ነው 7እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና ጽድቅንም ይወዳ፟ል ቅንነት ግን ፊቱን ታየዋለች