ለመዘምራን አለቃ ስለ ስምንተኛ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ አድነኝ ደግ ሰው አልቋልና ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሏልና 2ርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ በሽንገላ ከንፈር ኹለት ልብ ኾነው ይናገራሉ 3የሽንገላን ከንፈሮች ዅሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል ታላቅ ነገርን የምትናገረውን ምላስ 4ምላሳችንን እናበረታለን ከንፈራችን የእኛ ነው ጌታችን ማን ነው የሚሉትን 5ስለድኻዎች መከራ ስለችግረኛዎች ጩኸት እግዚአብሔር፦አኹን እነሣለኹ ይላል መድኀኒትን አደርጋለኹ በላዩም እገልጣለኹ 6በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው 7አቤቱ አንተ ጠብቀን ከዚችም ትውልድ ለዘለዓለም ታደገን 8በሰው ልጆች ዘንድ ምናምንቴ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ክፉዎች በዙሪያው ዅሉ ይመላለሳሉ