ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ እስከ መቼ ፈጽመኽ ትረሳኛለኽ እስከ መቼስ ፊትኽን ከእኔ ትሰውራለኽ 2እስከ መቼ በነፍሴ እመካከራለኹ ትካዜስ እስከ መቼ ዅልጊዜ ይኾናል እስከ መቼ ጠላቴ በላዬ ይጓደ ዳል 3አቤቱ አምላኬ እየኝ ስማኝም ጠላቴ አሸነፍኹት እንዳይል 4የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው ለሞትም እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ 5እኔ ግን በቸርነትኽ ታመንኹ ልቤም በመድኀኒትኽ ደስ ይለዋል 6የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለኹ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለኹ