ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1ሰነፍ በልቡ፦አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐሰቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም 2የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመ ለከተ 3ዅሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም አንድም ስንኳ የለም 4ጕረሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው በምላሳቸው ሸነገሉ 5ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቷል 6ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ የሰላምን መንገድ አላወቋ ትምና እግዚአብሔርን መፍራት በዐይናቸው ፊት የለም 7ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ ኀጢአት የሚሠሩ ዅሉ በእውኑ አያውቁምን እግዚአብሔርንም አይጠሩትም 8በዚያ በታላቅ ፍርሀት እጅግ ፈሩ እግዚአብሔር በጻድቃን ትውልድ ዘንድ ነውና 9የድኻዎችን ምክር አሳፈራችኹ እግዚአብሔር ግን ተስፋቸው ነው 10ከጽዮን መድኀኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ ያዕቆብ ደ ስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል