የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ በድንኳንኽ ውስጥ ማን ያድራል በተቀደሰውም ተራራኽ ማን ይኖራል 2በቅንነት የሚኼድ ጽድቅንም የሚያደርግ በልቡም እውነትን የሚናገር 3በአንደበቱ የማይሸነግል በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ ዘመዶቹንም የማይሰድብ 4ኀጢአተኛ በፊቱ የተናቀ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም 5ገንዘቡን በዐራጣ የማያበድር በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል እንዲህ የሚያደርግ ለዘለዓለም አይ ታወክም