የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ጸሎት።
1አቤቱ አንተ ለትውልድ ዅሉ መጠጊያ ኾንኽልን 2ተራራዎች ሳይወለዱ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ አንተ ነኽ 3ሰውን ወደ ኀሳር አትመልስም የሰው ልጆች ሆይ ተመለሱ ትላለኽ 4ሺሕ ዓመት በፊትኽ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን እንደ ሌሊትም ትጋት ነውና 5ዘመኖች የተናቁ ይኾናሉ በማለዳም እንደ ሣር ያልፋል 6ማልዶ ያብባል ያልፋልም በሠርክም ጠውልጎና ደርቆ ይወድቃል 7እኛ በቍጣኽ አልቀናልና በመዓትኽም ደንግጠናልና 8የተሰወረውን ኀጢአታችንን በፊትኽ ብርሃን በደላችንንም በፊትኽ አስቀመጥኽ 9ዘመናችን ዅሉ ዐልፏልና እኛም በመዓትኽ አልቀናልና ዘመኖቻችንም እንደ ሸረሪት ድር ይኾናሉ 10የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው ከእ ኛ ቶሎ ያልፋልና እኛም እንገሠጻለንና 11የቍጣኽን ጽናት ማን ያውቃል ከቍጣኽ ግርማ የተነሣ አለቁ 12በልብ ጥበብን እንድንማር ቀኝኽን እንዲህ አስታውቀን 13አቤቱ ተመለስ እስከ መቼስ ነው ስለ ባሪያዎችኽም ተሟገት 14በማለዳ ምሕረትኽን እንጠግባለን በዘመናችን ዅሉ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን 15መከራ ባሳየኸን ዘመን ፈንታ ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፋንታ ደስ ይለናል 16ባሪያዎችኽንና ሥራኽን እይ ልጆቻቸውንም ምራ 17የአምላካችን የእግዚአብሔር ብርሃን በላያችን ይኹን፦የእጆቻችንንም ሥራ በላያችን አቅና