የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር።
1መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራራዎች ናቸው 2ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳ፟ቸዋል 3የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ ባንቺ የተከበረ ነገር ይባላል 4የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን ዐስባቸዋለኹ እንሆ ፍልስጥኤማውያን ጢሮስም የኢትዮጵያም ሕዝብ እ ነዚህ በዚያ ተወለዱ 5ሰው እናታችን ጽዮን ይላል በውስጧም ሰው ተወለደ ርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት 6እግዚአብሔር ለሕዝቡ በውስጧም ለተወለዱት አለቃዎቿ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል 7ባንቺ የሚኖሩ ዅሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል