ለመዘምራን አለቃ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
1አቤቱ ለምድርኽ ሞገስን አደረግኽ የያዕቆብንም ምርኮ መለስኽ 2የሕዝብኽን ኀጢአት አስቀረኽ አበሳቸውንም ዅሉ ከደንኽ 3መዓትኽንም ዅሉ አስወገድኽ ከቍጣኽ መቅሠፍት ተመለስኽ 4የመድኀኒታችን አምላክ ሆይ መልሰን ቍጣኽንም ከእኛ መልስ 5በእውኑ ለዘለዓለም ትቈጣናለኽን ቍጣኽንስ ለልጅ ልጅ ታስረዝማለኽን 6አቤቱ ትመለሳለኽ ታድነንማለኽ ሕዝቡም ባንተ ደስ ይላቸዋል 7አቤቱ ምሕረትኽን አሳየን አቤቱ መድኀኒትኽንም ስጠን 8እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለኹ ሰላምን ለሕዝቡና ለቅዱሳኑ ልባቸውንም ወደ ርሱ ለሚመ ልሱ ይናገራልና 9ነገር ግን ክብር በምድራችን ያድር ዘንድ ማዳኑ ለሚፈሩት ቅርብ ነው 10ምሕረትና እውነት ተገናኙ ጽድቅና ሰላም ተስማሙ 11እውነት ከምድር በቀለች ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች 12እግዚአብሔርም በጎ ነገርን ይሰጣል ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች 13ጽድቅ በፊቱ ይኼዳል ፍለጋውንም በመንገድ ውስጥ ያኖራል