ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት የቆሬ ልጆች መዝሙር።
1የሰራዊት አምላክ ሆይ ማደሪያዎችኽ እንደምን የተወደዱ ናቸው! 2ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትወዳ፟ለች ትናፍቅማለች ልቤም ሥጋዬም በሕያው አምላክ ደስ ተሠ ኘ 3ወፍ ለርሷ ቤትን አገኘች ዋኖስም ጫጩቶቿን የምታኖርበት ቤት አገኘች የሰራዊት አምላክ ንጉሤም አ ምላኬም ሆይ ርሱ መሠዊያኽ ነው 4በቤትኽ የሚኖሩ ዅሉ የተመሰገኑ ናቸው ለዓለምና ለዘለዓለምም ያመሰግኑኻል 5አቤቱ ርዳታው ከአንተ ዘንድ የኾነለት በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው 6በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰነው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና 7ከኀይል ወደ ኀይል ይኼዳሉ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል 8የሰራዊት አምላክ አቤቱ ጸሎቴን ስማ የያዕቆብ አምላክ ሆይ አድምጥ 9አቤቱ መታመናችንን እይልን ወደ ቀባኸውም ፊት ተመልከት 10ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችኽ አንዲት ቀን ትሻላለች በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚ አብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥኹ 11እግዚአብሔር አምላክ ምሕረትንና እውነትን ስለ ወደደ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል እግዚአብሔር በቅ ንነት የሚኼዱትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም 12የሰራዊት አምላክ ሆይ ባንተ የታመነ ሰው ምስጉን ነው