የአሳፍ መዝሙር።
1እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል 2እስከ መቼ ሐሰትን ትፈርዳላችኹ እስከ መቼ ለኀጢአተኛዎች ፊት ታደላላችኹ 3ለድኻዎችና ለድኻ አደጎች ፍረዱ ለችግረኛውና ለምስኪኑ ጽድቅ አድርጉ 4ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ ከኀጢአተኛዎችም እጅ አስጥሏቸው 5አያውቁም አያስተውሉም በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ የምድር መሠረቶች ዅሉ ተናወጡ 6እኔ ግን፦አማልክት ናችኹ ዅላችኹም የልዑል ልጆች ናችኹ 7ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችኹ ከአለቃዎችም እንደ አንዱ ትወድቃላችኹ አልኹ 8አቤቱ ተነሥ በምድር ላይ ፍርድ አንተ አሕዛብን ዅሉ ትወርሳለኽና