ለመዘምራን አለቃ በመለከቶች ስለ አሦራውያን የአሳፍ የምስክር መዝሙር።
1ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ የእስራኤል ጠባቂ ሆይ አድምጥ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ ተገለጥ 2በኤፍሬምና በብንያም በምናሴም ኀይልኽን አንሣ እኛንም ለማዳን ና 3አቤቱ መልሰን ፊትኽንም አብራ እኛም እንድናለን 4የሰራዊት አምላክ አቤቱ በባሪያኽ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈጣለኽ 5የእንባ እንጀራን ትመግበናለኽ እንባም በስፍር ታጠጣናለኽ 6ለጎረቤቶቻችን ክርክር አደረግኸን ጠላቶቻችንም በላያችን ተሣለቁብን 7የሰራዊት አምላክ አቤቱ መልሰን ፊትኽንም አብራ እኛም እንድናለን 8ከግብጽ የወይን ግንድ አመጣኽ አሕዛብን አባረርኽ ርሷንም ተከልኽ 9በፊቷም ስፍራን አዘጋጀኽ ሥሮቿንም ተከልኽ ምድርንም ሞላች 10ጥላዋ ተራራዎችን ከደነ ጫፎቿም እንደእግዚአብሔር ዝግባ ኾኑ 11ቅርንጫፎቿንም እስከ ባሕር ቡቃያዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች 12ዐጥሯን ለምን አፈረስኽ መንገድ ዐላፊም ዅሉ ይቀጥፋታል 13የዱር ዕሪያ አረከሳት የአገር አውሬም ተሰማራባት 14የሰራዊት አምላክ ሆይ እንግዲህ ተመለስ ከሰማይ ተመልከት እይም ይህችንም የወይን ግንድ ጐብኝ 15በሰው ልጅ ለአንተ ያጸናኸውን ቀኝኽ የተከላትን አንሣ 16በእሳት ተቃጥላለች ተነቅላማለች ከፊትኽ ተግሣጽም የተነሣ ይጠፋሉ 17ለአንተ ባጸናኸው በሰው ልጅ ላይ በቀኝኽ ሰው ላይ እጅኽ ትኹን 18ከአንተም አንራቅ አድነን ስምኽንም እንጠራለን 19የሰራዊት አምላክ አቤቱ መልሰን ፊትኽንም አብራ እኛም እንድናለን