የአሳፍ መዝሙር።
1አቤቱ አሕዛብ ወደ ርስትኽ ገቡ የቅድስናኽንም መቅደስ አረከሱ ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጓ ት 2የባሪያዎችኽንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ የጻድቃንኽንም ሥራ ለምድር አራዊት 3ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውሃ አፈሰሱ የሚቀብራቸውም ዐጡ 4ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ኾን፟ በዙሪያችንም ላሉ ሣቅና ዘበት 5አቤቱ እስከ መቼ ለዘለዓለም ትቈጣለኽ ቅንአትኽም እንደ እሳት ይነዳ፟ል 6ስምኽን በማይጠሩ መንግሥታት ላይ በማያውቁኽም አሕዛብ ላይ መዓትኽን አፍስ፟ 7ያዕቆብን በልተውታልና ስፍራውንም ባድማ አድርገዋልና 8የቀደመውን በደላችንን አታስብብን ምሕረትኽ በቶሎ ታግኘን እጅግ ተቸግረናልና 9አምላካችንና መድኀኒታችን ሆይ ርዳን ስለስምኽ ክብር አቤቱ ታደገን ስለ ስምኽም ኀጢአታችንን አስ ተሰርይልን 10አሕዛብ አምላካቸው ወዴት ነው እንዳይሉ የፈሰሰውን የባሪያዎችኽን ደም በቀል በዐይኖቻችን ፊት አሕዛብ ያወቁ 11የእስረኛዎች ጩኸት ወደ ፊትኽ ይግባ እንደ ክንድኽም ታላቅነት ሊገደሉ የተፈረደባቸውን አድን 12አቤቱ የተዘባበቱብኽን መዘባበታቸውን ለጎረቤቶቻችን ሰባት ዕጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው 13እኛ ሕዝብኽ ግን የማሰማሪያኽም በጎች ለዘለዓለም እናመሰግንኻለን ለልጅ ልጅም ምስጋናኽን እንና ገራለን