ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች ስለ አሦራውያን የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።
1እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው 2ስፍራው በሳሌም ማደሪያውም በጽዮን ነው 3በዚያም የቀስትን ኀይል ጋሻን ሰይፍን ሰልፍንም ሰበረ በዚያም ቀንዶችን ሰበረ 4አንተ በዘለዓለም ተራራዎች ኾነኽ በድንቅ ታበራለኽ 5ልበ ሰነፎች ዅሉ ደነገጡ እንቅልፋቸውንም አንቀላፉ ባለጠጋዎች ዅሉ በእነርሱ እጅ ምንም አላገኙም 6የያዕቆብ አምላክ ሆይ ከተግሣጽኽ የተነሣ ፈረሰኛዎች ዅሉ አንቀላፉ 7አንተ ግን አንተ ግሩም ነኽ ቍጣኽን ማን ይቃወማል 8ፍርድን ከሰማይ አሰማኽ ምድር ፈራች ዝምም አለች 9ልበ የዋሃንን ያድን ዘንድ እግዚአብሔር ለፍርድ በተነሣ ጊዜ 10ሰው በፈቃዱ ያመሰግንኻልና ከኅሊናቸው ትርፍም በዓልኽን ያደርጋሉ 11ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ስእለትን ክፈሉ በዙሪያው ያሉ ዅሉ እጅ መንሻን ለሚያስፈራው ያገባሉ 12የመኳንንትን ነፍስ ያወጣል በምድርም ነገሥታት ዘንድ ያስፈራል