ለመዘምራን አለቃ አታጥፋ የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።
1አቤቱ እናመሰግንኻለን እናመሰግንኻለን ስምኽንም እንጠራለን ተኣምራትኽን ዅሉ እናገራለኹ 2ጊዜውን ስቀበል እኔ በቅን እፈርዳለኹ 3ምድርና በርሷ ውስጥ የሚኖሩት ዅሉ ቀለጡ እኔም ምሰሶዎቿን አጠናኹ 4ዐመፀኛዎችን፦አትበድሉ አልዃቸው ኀጢአተኛዎችንም፦ቀንዳችኹን አታንሡ 5ቀንዳችኹን እስከ ላይ አታንሡ በእግዚአብሔርም ላይ ዐመፅን አትናገሩ 6ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ ወይም ከምድረ በዳ የለምና 7እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ይህን ያዋርዳል ይህንም ያከብራል 8ጽዋ በእግዚአብሔር እጅ ነውና ያልተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሞላበት ከዚህ ወደዚያ አገላበጠው ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም የምድር ኀጢአተኛዎች ዅሉ ይጠጡታል 9እኔ ግን ለዘለዓለም ደስ ይለኛል ለያዕቆብም አምላክ ዝማሬን አቀርባለኹ 10የኃጥኣንን ቀንዶች ዅሉ እሰብራለኹ የጻድቃን ቀንዶች ግን ከፍ ከፍ ይላሉ