የአሳፍ ትምህርት።
1አቤቱ ስለ ምን ለዘወትር ጣልኸኝ በማሰማሪያኽ በጎች ላይስ ቍጣኽን ስለ ምን ተቈጣኽ 2አስቀድመኽ የፈጠርኻትን ማኅበርኽን የተቤዠኻትንም የርስትኽን በትር በርሷ ያደርኽባትን የጽዮንን ተራራ ዐስብ 3ጠላት በቅዱሳንኽ ላይ እንደ ከፋ፟ መጠን ዅልጊዜም በትዕቢታቸው ላይ እጅኽን አንሣ 4ጠላቶችኽ በበዓል መካከል ተመኩ የማያውቁትንም ምልክት ምልክታቸው አደረጉ 5እንደ ላይኛው መግቢያ ውስጥ በዱር እንዳሉም ዕንጨቶች በመጥረቢያ በሮቿን ሰበሩ 6እንዲሁ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰበሯት 7መቅደስኽን በእሳት አቃጠሉ የስምኽንም ማደሪያ በምድር ውስጥ አረከሱ 8አንድ ኾነው በልባቸው በየሕዝባቸው ኑ የእግዚአብሔርን በዓሎች ከምድር እንሻር አሉ 9ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ የለም እስከ መቼ እንዲኖር የሚያውቅ በኛ ዘንድ የ ለም 10አቤቱ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል ስምኽን ጠላት ዅልጊዜ ያቃልላልን 11ቀኝኽንም በብብትኽ መካከል እጅኽንም ፈጽመኽ ለምን ትመልሳለኽ 12እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው በምድርም መካከል መድኀኒትን አደረገ 13አንተ ባሕርን በኀይልኽ አጸናኻት አንተ የእባቦችን ራስ በውሃ ውስጥ ሰበርኽ 14አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥኽ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠኻቸው 15አንተ ምንጮቹንና ፈሳሾቹን ሰነጠቅኽ አንተ ዅልጊዜ የሚፈሱ፟ትን ወንዞች አደረቅኽ 16ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀኽ 17አንተ የምድርን ዳርቻ ዅሉ ሠራኽ በጋንም ክረምትንም አንተ አደረግኽ 18ይህን ፍጥረትኽን ዐስብ ጠላት እግዚአብሔርን ተላገደ ሰነፍ ሕዝብም ስሙን አስቈጣ 19የምትገዛልኽን ነፍስ ለአራዊት አትስጣት የችግረኛዎችኽን ነፍስ ለዘወትር አትርሳ 20ወደ ኪዳንኽ ተመልከት የምድር የጨለማ ስፍራዎች በኃጥኣን ቤቶች ተሞልተዋልና 21ችግረኛ ዐፍሮ አይመለስ ችግረኛና ምስኪን ስምኽን ያመሰግናሉ 22አቤቱ ተነሥ በቀልኽንም ተበቀል ሰነፎች ዅልጊዜም የተላገዱኽን ዐስብ 23የባሪያዎችኽን ቃል አትርሳ የጠላቶችኽ ኵራት ዅልጊዜ ወዳንተ ይወጣል