የአሳፍ መዝሙር።
1ልባቸው ለቀና ለእስራኤል እግዚአብሔር እንዴት ቸር ነው 2እኔ ግን እግሮቼ ሊሰናከሉ አረማመዴም ሊወድቅ ትንሽ ቀረ 3የኀጢአተኛዎችን ሰላም አይቼ በዐመፀኛዎች ቀንቼ ነበርና 4ለሞታቸው መጣጣር የለውምና ኀይላቸውም ጠንካራ ነውና 5እንደ ሰው በድካም አልኾኑም ከሰው ጋራም አልተገረፉም 6ስለዚህ ትዕቢት ያዛቸው ኀጢአትንና በደልን ተጐናጸፏት 7ዐይናቸው ስብ ስለ ኾነ ወጣ ልባቸውም ከምኞታቸው ይልቅ አገኘ 8ዐስበው ክፉ ነገርን ተናገሩ ከፍ ከፍ ብለውም በዐመፃ ተናገሩ 9አፋቸውን በሰማይ አኖሩ አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ 10ስለዚህ ሕዝቤ ወደዚህ ይመለሳሉ ፍጹም ጊዜም በላያቸው ይገኛል 11እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል በልዑልስ ዘንድ በእውኑ ዕውቀት አለ ይላሉ 12እንሆ እነዚህ ኀጢአተኛዎች ይደሰታሉ ዅልጊዜም ባለጠግነታቸውን ያበዛሉ 13እንዲህም አልኹ፦በእውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅኹ እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብኹ 14ዅልጊዜም የተገረፍኹ ኾንኹ መሰደቤም በማለዳ ነው 15እንደዚህ ብዬ ብናገር ኖሮ እንሆ የልጆችኽን ትውልድ በበደልኹ ነበር 16ዐውቅም ዘንድ ዐሰብኹ ይህ ግን በፊቴ ችግር ነበረ 17ወደእግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ ፍጻሜያቸውንም እስካስተውል ድረስ 18በድጥ ስፍራ አስቀመጥኻቸው ወደ ጥፋትም ጣልኻቸው 19እንዴት ለጥፋት ኾኑ! በድንገት አለቁ ስለ ኀጢአታቸውም ጠፉ 20ከሕልም እንደሚነቃ አቤቱ ስትነቃ ምልክታቸውን ታስነውራለኽ 21ልቤ ነዷ፟ልና ኵላሊቴም ቀልጧልና 22እኔ የተናቅኹ ነኝ አላውቅኹምም ባንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ኾንኹ 23እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋራ ነኝ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ 24ባንተ ምክር መራኸኝ ከክብር ጋራ ተቀበልኸኝ 25በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለኹ 26የልቤ አምላክ ሆይ ልቤና ሥጋዬ አለቀ እግዚአብሔር ግን ለዘለዓለም ዕድል ፈንታዬ ነው 27እንሆ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና ከአንተ ርቀው የሚያመነዝሩትንም ዅሉ አጠፋኻቸው 28ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናኽን ዅሉ እናገር ዘንድ