ስለ ሰሎሞን።
1አቤቱ ፍርድኽን ለንጉሥ ስጥ ጽድቅኽንም ለንጉሥ ልጅ 2ሕዝብኽን በጽድቅ ችግረኛዎችኽንም በፍርድ ይዳኝ ዘንድ 3ተራራዎችና ኰረብታዎች ለሕዝብኽ ሰላምን ይቀበሉ 4ለችግረኛዎች ሕዝብ በጽድቅ ትፈርዳለኽ የድኻዎችንም ልጆች ታድናለኽ ክፉውንም ታዋርደዋለኽ 5ፀሓይ በሚኖርበት ዘመን ዅሉ በጨረቃም ፊት ለፊት ለልጅ ልጅ ይኖራል 6እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ በምድርም ላይ እንደሚንጠባጠብ ጠብታ ይወርዳል 7በዘመኑም ጽድቅ ያብባል ጨረቃም እስኪያልፍ ድረስ ሰላም ብዙ ነው 8ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ ከወንዝም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይገዛል 9በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ ጠላቶቹም ዐፈር ይልሳሉ 10የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ የዐረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ 11ነገሥታት ዅሉ ይሰግዱለታል አሕዛብም ዅሉ ይገዙለታል 12ችግረኛውን ከቀማኛው እጅ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና 13ለችግረኛና ለምስኪን ይራራል የችግረኛዎችንም ነፍስ ያድናል 14ከግፍና ከጭንቀት ነፍሳቸውን ያድናል ስማቸው በፊቱ ክቡር ነው 15ርሱ ይኖራል ከዐረብም ወርቅ ይሰጡታል ዅልጊዜም ወደ ርሱ ይጸልያሉ ዘወትርም ይባርኩታል 16በምድር ውስጥ በተራራዎች ላይ መጠጊያ ይኾናል ፍሬውም ከሊባኖስ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል እንደምድ ር ሣር በከተማ ይበቅላል 17ስሙ ለዘለዓለም ቡሩክ ይኾናል ከፀሓይም አስቀድሞ ስሙ ይኖራል የምድር አሕዛብ ዅሉ በርሱ ይባረ ካሉም አሕዛብ ዅሉ ያመሰግኑታል 18ብቻውን ተኣምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ 19የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘለዓለም ይባረክ ምስጋናውም ምድርን ዅሉ ይምላ ይኹን ይኹን 20የእሴይ ልጅ የዳዊት መዝሙር ተፈጸመ