አስቀድመው ስለ ተማረኩ ስለ አሚናዳብ ልጆች የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ አንተን ታመንኹ ለዘለዓለም አልፈር 2በጽድቅኽ አስጥለኝ ታደገኝም ዦሮኽን ወደ እኔ አዘንብል አድነኝም 3በጠንካራ ቦታ ታድነኝ ዘንድ አምላክና መሸሸጊያ ኹነኝ ኀይሌ መጠጊያዬ አንተ ነኽና 4አምላኬ ከኀጢአተኛ እጅ ከዐመፀኛና ከግፈኛም እጅ አድነኝ 5አቤቱ አንተ ተስፋዬ ነኽና እግዚአብሔር ሆይ ከታናሽነቴ ዠምረኽ መታመኛዬ ነኽና 6ከማሕፀን ዠምሮ ባንተ ተደገፍኹ ከእናቴም ሆድ ዠምሮ አንተ መሸሸጊያዬ ነኽ ዅልጊዜም ዝማሬዬ ለአ ንተ ነው 7ለብዙዎች መደነቂያ ኾንኹ አንተ ግን ብርቱ መጠጊያዬ ነኽ 8አፌን ምስጋና ምላ ዅልጊዜ ክብርኽንና ግርማኽን እዘምር ዘንድ 9በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ ጕልበቴም ባለቀ ጊዜ አትተወኝ 10ጠላቶቹ በላዬ ተናግረዋልና ነፍሴንም የሚሿት በአንድነት ተማክረዋልና እንዲህም አሉ 11እግዚአብሔር ትቶታል የሚያድነው የለምና ተከትላችኹ ያዙት 12አምላክ ሆይ ከእኔ አትራቅ አምላኬ ሆይ እኔን ለመርዳት ፍጠን 13ነፍሴን የሚቃወሟት ይፈሩ ይጥፉም ጕዳቴንም የሚፈልጉ ዕፍረትንና ኃሣርን ይልበሱ 14እኔ ግን ዅልጊዜ ተስፋ አደርጋለኹ በምስጋናኽም ዅሉ ላይ እጨምራለኹ 15ሥራን አላውቅምና አፌ ጽድቅኽን ዅልጊዜም ማዳንኽን ይናገራል 16በእግዚአብሔር ኀይል እገባለኹ አቤቱ ጽድቅኽን ብቻ ዐስባለኹ 17አምላኬ ከታናሽነቴ ዠምረኽ አስተማርኸኝ እስከ ዛሬም ተኣምራትኽን እነግራለኹ 18እስካረጅም እስክሸመግልም ድረስ ለሚመጣ ትውልድም ዅሉ ክንድኽን ኀይልኽንም ጽድቅኽንም እስክነግ ር ድረስ አቤቱ አትተወኝ 19አቤቱ እስከ አርያም ታላላቅ ነገሮችን አደረግኽ አምላክ ሆይ እንደ አንተ ያለ ማን ነው 20ብዙ ጭንቀትንና መከራን አሳይተኸኛልና ተመለስኽ ሕያውም አደረግኸኝ ከምድር ጥልቅም እንደ ገና አወጣኸኝ 21ጽድቅኽንም አብዛው ተመልሰኽም ደስ አሠኘኝ ከጥልቅም እንደ ገና አወጣኸኝ 22እኔም በበገና ስለ እውነትኽ አመሰግንኻለኹ የእስራኤል ቅዱስ አምላክ ሆይ በመሰንቆ እዘምርልኻለ ኹ 23ዝማሬን ባቀርብኹልኽ ጊዜ ከንፈሮቼ ደስ ይላቸዋል አንተ ያዳንኻትም ነፍሴ 24ጕዳቴን የሚሹ ባፈሩና በተነወሩ ጊዜ አንደበቴ ደግሞ ዅልጊዜ ጽድቅኽን ይናገራል