ለመዘምራን አለቃለመታሰቢያ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ እኔን ለማዳን ተመልከት አቤቱ እኔን ለመርዳት ፍጠን 2ነፍሴን የሚሿት ይፈሩ ይጐስቍሉም ክፉንም የሚመክሩብኝ ወደ ዃላቸው ይመለሱ ይፈሩም 3እንኳ! እንኳ! የሚሉኝ ዐፍረው ወዲያው ወደ ዃላቸው ይመለሱ 4የሚሹኽ ዅሉ ባንተ ሐሤት ያድርጉ ደስ ይበላቸው ማዳንኽን የሚወዱ ዅልጊዜ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበሉ 5እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ አቤቱ ርዳኝ ረዳቴ ታዳጊዬም አንተ ነኽ አቤቱ አትዘግይ