ለመዘምራን አለቃ የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
1እግዚአብሔር ይነሣ ጠላቶቹም ይበተኑ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ 2ጢስ እንደሚበን፟ እንዲሁ ይብነኑ ሠም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ እንዲሁ ኃጥኣን ከእግዚአብሔር ፊ ት ይጥፉ 3ጻድቃንም ደስ ይበላቸው በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ በደስታም ደስ ይበላቸው 4ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም ዘምሩ ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ ስሙ እግዚአብሔር ነው በፊቱም ደስ ይበላችኹ በፊቱም ይደነግጣሉ 5እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው ለድኻ አደጎች አባት ለባልቴቶችም ዳኛ ነው 6እግዚአብሔር ብቸኛዎችን በቤት ያሳድራቸዋል እስረኛዎችንም በኀይሉ ያወጣቸዋል ዐመፀኛዎች ግን በም ድረ በዳ ይኖራሉ 7አቤቱ በሕዝብም ፊት በወጣኽ ጊዜ በምድረ በዳም ባለፍኽ ጊዜ ምድር ተናወጠች 8ከሲና አምላክ ፊት ከእስራኤል አምላክ ፊት ሰማያትም አንጠበጠቡ 9አቤቱ የሞገስን ዝናብ ለርስትኽ አዘነብኽ በደከመም ጊዜ አንተ አጸናኸው 10እንስሳዎችኽ በውስጡ ዐደሩ አቤቱ በቸርነትኽ ለድኻዎች አዘጋጀኽ 11እግዚአብሔር ቃሉን ሰጠ የሚያወሩት ብዙ ሰራዊት ናቸው 12የሰራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ በቤትም የምትኖር ምርኮን ተካፈለች 13በርስቶች መካከል ብታድሩ ከብር እንደ ተሠሩ እንደ ርግብ ክንፎች በቅጠልያ ወርቅም እንደ ተለበ ጡ ላባዎቿ ትኾናላችኹ 14ሰማያዊ ንጉሥ በላይዋ ባዘዘ ጊዜ በሰልሞን ላይ በረዶ ዘነበ 15የእግዚአብሔር ተራራ የለመለመ ተራራ ነው የጸና ተራራና የለመለመ ተራራ ነው 16የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ እግዚአብሔር ይህን ተራራ ያድርበት ዘንድ ወደደው በእውነት እግዚ አብሔር ለዘለዓለም ያድርበታል 17የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሺሕ ናቸው ጌታ በመቅደሱ በሲና በመካከላቸው ነው 18ወደ ላይ ዐረግኽ ምርኮን ማረክኽ ስጦታንም ለሰዎች ሰጠኽ ደግሞም ለዐመፀኛዎች በዚያ ያድሩ ዘን ድ 19እግዚአብሔር አምላክ ቡሩክ ነው እግዚአብሔር በየዕለቱ ቡሩክ ነው የመድኀኒታችን አምላክ ይረዳና ል 20አምላካችንስ የደኅንነት አምላክ ነው ከሞት መውጣትም ከእግዚአብሔር ነው 21ነገር ግን እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ በኀጢአት የሚኼድንም የጠጕሩን ዐናት ይቀጠቅጣል 22እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ከባሳን አመጣቸዋለኹ ከባሕርም ጥልቅ እመልሳቸዋለኹ 23እግሮችኽ በደም ይረገጡ ዘንድ የውሻዎችኽ ምላስ በጠላቶች ላይ ይኾን ዘንድ 24የአምላኬ የንጉሥ መንገድ በመቅደሱ አቤቱ መንገድኽ ተገለጠ 25አለቃዎች ቀደሙ መዘምራንም ተከተሉ ከበሮን በሚመቱ በቈነዣዥት መካከል 26እግዚአብሔርን በጉባኤ ጌታችንንም በእስራኤል ምንጭ አመስግኑት 27ወጣቱ ብንያም በጕልበቱ በዚያ አለ ገዢዎቻቸው የይሁዳ አለቃዎች የዛብሎን አለቃዎችና የንፍታሌም ም አለቃዎች 28አቤቱ ኀይልኽን እዘዝ አቤቱ ይህንም ለእኛ የሠራኸውን አጽናው 29በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስኽ ነገሥታት እጅ መንሻን ለአንተ ያመጣሉ 30በሸምበቆ ውስጥ ያሉትን አራዊት በአሕዛብ ውስጥ ያሉትን የበሬዎችንና የወይፈኖችን ጉባኤ ገሥጽ እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ ሰልፍን የሚወዱትን አሕዛብን በትናቸው 31መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች 32የምድር ነገሥታት ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለጌታም ዘምሩ 33በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ የኀይል ቃል የኾነ ቃሉን እንሆ ይሰጣል 34ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ ግርማው በእስራኤል ላይ ኀይሉም በደመናት ላይ ነው 35እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው የእስራኤል አምላክ ርሱ ኀይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣ ል እግዚአብሔርም ይመስገን