ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም ፊቱንም በላያችን ያብራ 2በአሕዛብ ዅሉ መካከል ማዳንኽን መንገድኽንም በምድር እናውቅ ዘንድ 3አቤቱ አሕዛብ ያመስግኑኽ አሕዛብ ዅሉ ያመስግኑኽ 4ለአሕዛብ በቅን ትፈርድላቸዋለኽና አሕዛብንም በምድር ላይ ትመራለኽና አሕዛብ ደስ ይበላቸው ሐሤት ም ያድርጉ 5አቤቱ አሕዛብ ያመስግኑኽ አሕዛብ ዅሉ ያመስግኑኽ 6ምድር ፍሬዋን ሰጠች እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል 7እግዚአብሔር ይባርከናል የምድርም ዳርቻ ዅሉ ይፈሩታል