ለመዘምራን አለቃ የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
1አቤቱ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገ፟ባ፟ል ለአንተም ጸሎት ይቀርባል 2ሥጋ ዅሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወዳንተ ይመጣል 3የዐመፃ ነገር በረታብን ኀጢአታችንንስ አንተ ይቅር ትላለኽ 4አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችኽም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው ከቤትኽ በረከት እንጠግባለን 5ቤተ መቅደስኽ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው በምድር ዳርቻ ዅሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋ ቸው የኾንኽ አምላካችንና መድኀኒታችን ሆይ ስማን 6በጕልበትኽ ተራራዎችን አጸናኻቸው በኀይልም ታጥቀኻል 7የባሕሩን ጥልቀት የሞገድንም ጩኸት ታናውጣለኽ 8ከተኣምራትኽ የተነሣ አሕዛብ ይደነግጣሉ በምድር ዳርቻም የሚኖሩ ይፈራሉ የጧትንና የማታን መውጫ ደስ ታሠኛቸዋለኽ 9ምድርን ጐበኘኻት አጠጣኻትም ብልጥግናዋንም እጅግ አበዛኽ የእግዚአብሔርን ወንዝ ውሃን የተመላ ነ ው ምግባቸውን አዘጋጀኽ እንዲሁ ታሰናዳለኽና 10ትልሟን ታረካለኽ ቦይዋንም ታስተካክላለኽ በነጠብጣብ ታለሰልሳታለኽ ቡቃያዋንም ትባርካለኽ 11በቸርነትኽ ዓመትን ታቀዳጃለኽ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል 12የምድረ በዳ ተራራዎች ይረካሉ ኰረብታዎችም በደስታ ይታጠቃሉ 13ማሰማሪያዎች መንጋዎችን ለበሱ ሸለቆዎችም በእኽል ተሸፈኑ በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉም