ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ ወዳንተ በለመንኹ ጊዜ ጸሎቴን ስማኝ ከጠላትም ፍርሀት ነፍሴን አድን 2ከክፉዎች ሸንጎ ከዐመፀኛዎችም ብዛት ሰውረኝ 3እንደ ሰይፍ ምላሳቸውን አሰሉ መራራ ነገርን ለማድረግ 4ንጹሕንም በስውር ለመንደፍ ቀስትን ገተሩ ድንገት ይነድፉታል አይፈሩምም 5ለእነርሱ ለራሳቸው ክፉ ነገርን አጸኑ ወጥመድን ይሰውሩ ዘንድ ተማከሩ ማንስ ያየናል ይላሉ 6ዐመፃን ፈልጓት ሲፈትኑም አለቁ የሰው የውስጥ ዐሳቡና ልቡ የጠለቀ ነው 7እግዚአብሔርም ከፍ ከፍ ይላል የድንገትም ፍላጻ ያቈስላቸዋል 8አንደበታቸው ያሰናክላቸዋል የሚያይዋቸውም ዅሉ ይደነግጣሉ 9ሰዎች ዅሉ ፈሩ የእግዚአብሔርንም ሥራ ተናገሩ ሥራውንም አስተዋሉ 10ጻድቅ በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል በርሱም ይታመናል ልባቸውም የቀና ዅሉ እልል ይላሉ