በኤዶምያስ ምድረ በዳ በነበረ ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1አምላኬ አምላኬ ወዳንተ እገሠግሣለኹ ነፍሴ አንተን ተጠማች ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች ዕንጨት ና ውሃ በሌለበት በምድረ በዳ 2ኀይልኽንና ክብርኽን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትኹኽ 3ምሕረትኽ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑኻል 4እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንኻለኹ ባንተም ስም እጆቼን አነሣለኹ 5ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች ከንፈሮቼም ስምኽን በደስታ ያመሰግናሉ 6በመኝታዬም ዐስብኻለኹ በማለዳም እናገርልኻለኹ 7ረዳቴ ኾነኸኛልና በክንፎችኽም ጥላ ደስ ይለኛልና 8ነፍሴ በዃላኽ ተከታተለች እኔንም ቀኝኽ ተቀበለችኝ 9እነርሱ ግን ነፍሴን ለከንቱ ፈለጓት ወደ ምድር ጥልቅ ይገባሉ 10ለሰይፍ እጅ ዐልፈው ይሰጣሉ የቀበሮም ዕድል ፈንታ ይኾናሉ 11ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል በርሱ የሚምል ዅሉ ይከብራል ሐሰትን የሚናገር አፍ ይዘጋ ልና