ለመዘምራን አለቃ ስለ ኤዶታም የዳዊት መዝሙር።
1ነፍሴ ለእግዚአብሔር የምትገዛ አይደለችምን መድኀኒቴ ከርሱ ዘንድ ናትና 2ርሱ አምላኬ መድኀኒቴም ነውና ርሱ መጠጊያዬ ነው እጅግም አልታወክም 3እስከ መቼ በሰው ላይ ትቆማላችኹ እናንተ ዅላችኹ እንዳዘነበለ ግድግዳ እንደ ፈረሰም ቅጥር ትገድ ላላችኹ 4ነገር ግን ክብሬን ይሽሩ ዘንድ መከሩ ሐሰትንም ይወዳ፟ሉ በአፋቸው ይባርካሉ በልባቸውም ይረግማሉ 5ነገር ግን ነፍሴ ሆይ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ ተስፋዬ ከርሱ ዘንድ ናትና 6ርሱ አምላኬ መድኀኒቴም ነውና ርሱ መጠጊያዬ ነው አልታወክም 7መድኀኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው የረድኤቴ አምላክ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው 8የሕዝብ ማኅበር ዅላችኹ በርሱ ታመኑ ልባችኹንም በፊቱ አፍሱ፟ እግዚአብሔር ረዳታችን ነው 9ነገር ግን የሰው ልጆች ከንቱ ናቸው የሰው ልጆችም ሐሰተኛዎች ናቸው በሚዛንም ይበድላሉ እነርሱስ በፍጹም ከንቱ ናቸው 10ዐመፃን ተስፋ አታድርጉ ቅሚያንም አትተማመኑት ባለጠግነት ቢበዛ ልባችኹ አይኵራ 11እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ እኔም ይህን ብቻ ሰማኹ ኀይል የእግዚአብሔር ነው 12አቤቱ ምሕረትም ያንተ ነው አንተ ለያንዳንዱ እንደ ሥራው ፍዳውን ትሰጣለኽና