ለመዘምራን አለቃ አታጥፋ። ሳኦል ይገድሉት ዘንድ ቤቱን እንዲጠብቁ በላከ ጊዜ የዳዊት ቅኔ።
1አምላኬ ሆይ ከጠላቶቼ አድነኝ በላዬም ከቆሙት አስጥለኝ 2ከግፍ አድራጊዎች ታደገኝ ከደም ሰዎችም አድነኝ 3እንሆ ነፍሴን ሸምቀውባታልና ብርቱዎችም በላዬ ተሰበሰቡ አቤቱ በበደሌም አይደለም በኀጢአቴም አይ ደለም 4ያለበደል ሮጥኹ ተዘጋጀኹም ተነሥ ተቀበለኝ እይም 5አንተም አቤቱ የኀያላን አምላክ የእስራኤል አምላክ አሕዛብን ዅሉ ትጐበኛቸው ዘንድ ተነሥ ዐመፅ የሚያደርጉትን ዅሉ አትማራቸው 6ማታ ይመለሱ እንደ ውሻዎችም ይራቡ በከተማም ይዙሩ 7እንሆ በአፋቸው አሰምተው ይናገራሉ ሰይፍም በከንፈሮቻቸው አለ ማን ይሰማል ይላሉ 8አንተ ግን አቤቱ ትሥቅባቸዋለኽ አሕዛብንም ዅሉ ትንቃቸዋለኽ 9እግዚአብሔር መጠጊያዬ ነውና ኀይሌን ወዳንተ አስጠጋለኹ 10የአምላኬ ቸርነቱ ይገናኘኛል አምላኬ በጠላቶቼ ላይ ያሳየኛል 11ሕግኽን እንዳይረሱ አትግደላቸው አቤቱ ጋሻዬ በኀይልኽ በትናቸው አውርዳቸውም 12ስለአፋቸው ኀጢአት ስለከንፈራቸውም ቃል መርገምንና ሐሰትን ስለሚናገሩ በትዕቢታቸው ይጠመዱ 13በቍጣ አጥፋቸው እንዳይኖሩም አጥፋቸው የያዕቆብም አምላክ እስከምድር ዳርቻ ድረስ እንዲገዛ ይወ ቁ 14ማታ ይመለሱ እንደ ውሻዎችም ይራቡ በከተማም ይዙሩ 15እነርሱም መብል ለመፈለግ ይበተኑ ያልጠገቡ እንደ ኾነም ያንጐረጕራሉ 16እኔ ግን ለኀይልኽ እቀኛለኹ በምሕረትኽም ማልዶ ደስ ይለኛል በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና ዐምባዬ ኾነኸኛልና 17ረዳቴ ሆይ ለአንተ ለአምላኬ እዘምራለኹ አንተ አምላኬ መጠጊያዬ ምሕረቴም ነኽና