ለመዘምራን አለቃ አታጥፋ። የዳዊት ቅኔ።
1በእውነት ጽድቅን ብትናገሩስ የሰው ልጆች ሆይ በቅን ትፈርዳላችኹ 2በልባችኹ በምድር ላይ ኀጢአትን ትሠራላችኹና እጆቻችኹም ግፍን ይታታሉና 3ኃጥኣን ከማሕፀን ዠምረው ተለዩ ከሆድም ዠምረው ሳቱ ሐሰትንም ተናገሩ 4ቍጣቸው እንደ እባብ መርዝ ነው እንደምድር አውሬም ዦሮዋ የተደፈነ ነው 5ዐዋቂ ሲደግምባት የአስማተኛውን ቃል እንደማትሰማ 6እግዚአብሔር ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ይሰብራል እግዚአብሔር የአንበሳዎቹን መንጋጋቸውን ያደቃ፟ ል 7እንደሚፈስ፟ ውሃ ይቀልጣሉ እስኪያደክማቸው ድረስ ፍላጻዎቹን ይገትራል 8እንደሚቀልጥ ሠም ያልቃሉ እሳት ወደቀች ፀሓይንም አላይዋትም 9እሾኻችኹ ሳይታወቅ በትር ኾነ ሕያዋን ሳላችኹ በመዓቱ ይነጥቃችዃል 10ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል በኀጢአተኛው ደምም እጁን ይታጠባል 11ሰውም፦በእውነት ለጻድቅ ፍሬ አለው በእውነት በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ ይላል