ለመዘምራን አለቃ አታጥፋ። ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በዋሻ በነበረበት ጊዜ የዳዊት ቅኔ።
1ማረኝ አቤቱ ማረኝ ነፍሴ አንተን ታምናለችና ጕዳት እስክታልፍ ድረስ በክንፎችኽ ጥላ እታመናለኹ 2ወደሚረዳኝ እግዚአብሔር ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጮኻለኹ 3ከሰማይ ልኮ አዳነኝ ለረገጡኝም ውርደትን ሰጣቸው እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነቱን ላከ 4ነፍሴን ከአንበሳዎች መካከል አዳናት ደንግጬ ተኛኹ የሰው ልጆች ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ አንደበታቸ ው የተሳለ ሾተል ነው 5አምላክ ሆይ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል ክብርኽም በምድር ዅሉ ላይ ትኹን 6ለእግሮቼ ወጥመድን አዘጋጁ ነፍሴንም አጐበጧት ጕድጓድ በፊቴ ቈፈሩ በርሱም ወደቁ 7ልቤ ጨካኝ ነው አቤቱ ልቤ ጨካኝ ነው እቀኛለኹ እዘምራለኹ 8ክብሬ ይነሣ በገናና መሰንቆም ይነሡ እኔም ማልጄ እነሣለኹ 9አቤቱ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንኻለኹ በወገኖችም ዘንድ እዘምርልኻለኹ 10ምሕረትኽ እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ብላለችና እውነትኽም እስከ ደመናት ድረስ 11አምላክ ሆይ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል ክብርኽም በምድር ዅሉ ላይ ትኹን