ለመዘምራን አለቃ ከቅዱሳን ስለ ራቁ ሕዝብ ፍልስጥኤማውያን በጌት በያዙት ጊዜ የዳዊት ቅኔ።
1አቤቱ ሰው ረግጦኛልና ማረኝ ዅልጊዜም በሰልፍ አስጨንቆኛል 2የሚዋጉኝ በዝተዋልና ዅልጊዜ ቀኑን ዅሉ ጠላቶቼ ረገጡኝ 3እኔ ግን ፈራኹ ባንተም ታመንኹ 4በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለኹ በእግዚአብሔር ታመንኹ አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል 5ዅልጊዜ ቃሎቼን ያጸይፉብኛል በእኔ ላይም የሚመክሩት ዅሉ ለክፉ ነው 6ይሸምቁብኛል ይሸሽጉኝማል እነርሱም ተረከዜን ይመለካከታሉ ዅልጊዜም ነፍሴን ይሸምቁባታል 7በምንም ምን አታድናቸውም አሕዛብን በቍጣ ትጥላቸዋለኽ 8አምላክ ሆይ ሕይወቴን ነገርኹኽ እንባዬን እንደ ትእዛዝኽ በፊትኽ አኖርኽ 9በጠራኹኽ ጊዜ ጠላቶቼ ወደ ዃላቸው ይመለሳሉ አንተ አምላኬ እንደ ኾንኽ እንሆ ዐወቅኹ 10በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለኹ በእግዚአብሔር ቃሉን አከብራለኹ 11በእግዚአብሔር ታመንኹ አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል 12አቤቱ የምስጋና ስእለት የምሰጥኽ ከእኔ ዘንድ ነው 13ነፍሴን ከሞት እግሮቼን ከመውደቅ አድነኻልና በሕያዋን ብርሃን እግዚአብሔርን ደስ አሠኘው ዘንድ