ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች የዳዊት ትምህርት።
1አቤቱ ጸሎቴን አድምጥ ልመናዬንም ቸል አትበል 2ተመልከተኝ ስማኝም በሐዘኔ ተቅበዘበዝኹ ተናወጥኹም 3ከጠላት ድምፅ ከዐመፀኛም ግፍ የተነሣ ዐመፃን በላዬ ጥለውብኛልና በቍጣም ጠልተውኛልና 4ልቤ በላዬ ተናወጠብኝ የሞት ድንጋጤም ወደቀብኝ 5ፍርሀትና እንቅጥቅጥ መጡብኝ ጨለማም ሸፈነኝ 6በርሬ ዐርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክንፍን ማን በሰጠኝ! 7እንሆ ኰብልዬ በራቅኹ በምድረ በዳም በተቀመጥኹ 8ከዐውሎና ከብርቱ ነፋስ ሸሽቼ በፈጠንኹ አልኹ 9አቤቱ ግፍንና ጠብን በከተማ ውስጥ አይቻለኹና አስጥማቸው አንደበታቸውንም ቍረጥ 10በቀንና በሌሊት በቅጥሯ ይከቧ፟ታል ዐመፃና ድካም ኀጢአትም በመካከሏ ነው 11ተንኰልና ሽንገላ ከአደባባይዋ አይርቁም 12ጠላትስ ቢሰድበኝ በታገሥኹ ነበር የሚጠላኝም ራሱን በላዬ ከፍ ከፍ ቢያደርግ ከርሱ በተሸሸግኹ ነበር 13አንተ ግን እኩያዬ ሰው ባልንጀራዬና የልቤ ወዳጅ 14መብልን ከእኔ ጋራ በአንድነት ያጣፈጥኽ ባንድ ልብ በእግዚአብሔር ቤት ተራመድን 15ሞት ይምጣባቸው በሕይወት ሳሉ ወደ ሲኦል ይውረዱ ክፋት በማደሪያቸውና በመካከላቸው ነውና 16እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር ጮኽኹ እግዚአብሔርም ሰማኝ 17በማታና በጧት በቀትርም እናገራለኹ እጮኽማለኹ ቃሌንም ይሰማኛል 18በእኔ ላይ ብዙ ነበሩና ከሚቃረቡኝ ነፍሴን በሰላም አድናት 19ቤዛ የላቸውምና እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና ከጥንት ዠምሮ የነበረ እግዚአብሔር ሰምቶ ያጐሰቍላ ቸዋል 20ከርሱ ጋራ ሰላም በነበሩት ላይ እጁን ዘረጋ ኪዳኑንም አረከሱ 21አፉ ከቅቤ ይልቅ ለዘበ በልቡ ግን ሰልፍ ነበረ ቃሎቹም ከዘይት ይልቅ ለሰለሱ እነርሱ ግን እን ደ ተመዘዘ ሰይፍ ናቸው 22ትካዜኽን በእግዚአብሔር ላይ ጣል ርሱም ይደግፍኻል ለጻድቁም ለዘለዓለም ሁከትን አይሰጠውም 23አንተ ግን አቤቱ ወደሞት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለኽ የደም ሰዎችና ሸንጋዮች ዘመናቸው ግማሽ አይሞላ ም እኔ ግን አቤቱ እታመንኻለኹ