ለመዘምራን አለቃ በማኸላት የዳዊት መዝሙር ፍጻሜ።
1ሰነፍ በልቡ፦አምላክ የለም ይላል ረከሱ በበደላቸውም ጐሰቈሉ በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም 2የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመ ለከተ 3ዅሉ በደሉ ዐብረውም ረከሱ አንድ ስንኳ በጎን ነገር የሚያደርጋት የለም 4ሕዝቤን እንጀራ እንደሚበላ የሚበሉ ግፍ አድራጊዎች ዅሉ አያውቁምን እግዚአብሔርንም አይጠሩትም 5እግዚአብሔር የግብዞችን ዐጥንቶች በትኗልና በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅግ ፈሩ እግዚአብሔር ንቋ ቸዋልና አሳፈርኻቸው 6መድኀኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን በሰጠ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል