ለመዘምራን አለቃ ዶይቅ ኤዶማዊው መጥቶ ለሳኦል፦ ዳዊት ወደ አቤሜሌክ ቤት መጥቶአል ብሎ በነገረው ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1ኀያል ሆይ በክፋት ለምን ትጓደዳለኽ ዅልጊዜስ በመተላለፍ 2አንደበትኽ ኀጢአትን ያስባል እንደ ተሳለ ምላጭ ሽንገላን አደረግኽ 3ከመልካም ይልቅ ክፋትን ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዐመፃን ወደድኽ 4የሚያጠፉ ቃልን ዅሉ የሽንገላ ምላስን ወደድኽ 5ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስኻል ከቤትኽም ይነቅልኻል ያፈልስኻልም ሥርኽንም ከሕያዋን ምድር 6ጻድቃን አይተው ይፈራሉ በርሱም ይሥቃሉ እንዲህም ይላሉ፦ 7እግዚአብሔርን ረዳቱ ያላደረገ በባለጠግነቱም ብዛት የታመነ በከንቱ ነገርም የበረታ ያ ሰው እንሆ 8እኔስ በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለመለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ ለዓለምና ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ምሕረት ታመንኹ 9አድርገኽልኛልና ለዘለዓለም አመሰግንኻለኹ በቅዱሳንኽም ዘንድ መልካም ነውና ስምኽን ተስፋ አደርጋ ለኹ