የአሳፍ መዝሙር።
1የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ ከፀሓይም መውጫ ዠምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ምድርን ጠራ ት 2ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ኾኖ ይመጣል 3አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊት ይቃጠላል በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ 4በላይ ያለውን ሰማይን ምድርንም በሕዝቡ ለመፍረድ ይጠራል 5ከርሱ ጋራ ለመሥዋዕት ኪዳን የቆሙትን ቅዱሳኑን ሰብስቡለት 6ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና 7ሕዝቤ ስማኝ ልንገርኽ እስራኤልም ስማኝ ልመስክርብኽ አምላክስ እኔ አምላክኽ ነኝ 8ስለ ቍርባንኽ የምዘልፍኽ አይደለኹም የሚቃጠል መሥዋዕትኽ ዅልጊዜ በፊቴ ነው 9ከቤትኽ ፍሪዳን ከመንጋኽም አውራ ፍየልን አልወስድም 10የምድረ በዳ አራዊት ዅሉ በሺሕ ተራራዎች ያሉ እንስሳዎችም የእኔ ናቸውና 11የሰማይን አዕዋፍ ዅሉ ዐውቃለኹ የምድረ በዳ አራዊትም በእኔ ዘንድ ናቸው 12ብራብም ለአንተ አልነግርኽም ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና 13የፍሪዳውን ሥጋ እበላለኹን የፍየሉንስ ደም እጠጣለኹን 14ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ ለልዑልም ስእለትኽን ስጥ 15በመከራ ቀን ጥራኝ አድንኽማለኹ አንተም ታከብረኛለኽ 16ኀጢአተኛውን ግን እግዚአብሔር አለው፦ለምን አንተ ሕጌን ትናገራለኽ ኪዳኔንም በአፍኽ ለምን ትወ ስዳለኽ 17አንተስ ተግሣጼን ጠላኽ ቃሎቼንም ወደ ዃላኽ ጣልኽ 18ሌባውን ባየኽ ጊዜ ከርሱ ጋራ ትሮጥ ነበር ዕድል ፈንታኽንም ከአመንዝራዎች ጋራ አደረግኽ 19አፍኽ ክፋትን አበዛ አንደበትኽም ሽንገላን ተበተበ 20ተቀምጠኽ ወንድምኽን ዐማኸው ለእናትኽም ልጅ ዕንቅፋት አኖርኽ 21ይህን አድርገኽ ዝም አልኹኽ እኔ እንደ አንተ እኾን ዘንድ ጠረጠርኽ እዘልፍኻለኹ በፊትኽም እቆ ማለኹ 22እግዚአብሔርን የምትረሱ እናንተ ይህን አስተውሉ አለዚያ ግን ይነጥቃል የሚያድንም የለም 23ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል የእግዚአብሔርን ማዳን ለርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ