ለመዘምራን አለቃ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
1አሕዛብ ዅላችኹ ይህን ስሙ በዓለም የምትኖሩትም ዅላችኹ አድምጡ 2ዝቅተኛዎችና ከፍተኛዎች ባለጠጋዎችና ድኻዎች በአንድነት 3አፌ ጥበብን ይናገራል የልቤም ዐሳብ ማስተዋልን 4ዦሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለኹ በበገናም ምስጢሬን እገልጣለኹ 5ኀጢአት ተረከዜን በከበበኝ ጊዜ በክፉ ቀን ለምን እፈራለኹ 6በኀይላቸው የሚታመኑ በባለጠግነታቸውም ብዛት የሚመኩ 7ወንድም ወንድሙን አያድንም ሰውም አያድንም ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም 8-9 ለዘለዓለም እንዲኖር ጥፋትንም እንዳያይ የነፍሳቸው ለውጥ ከብሯልና ለዘለዓለምም ቀርቷልና 10ብልኀተኛዎች እንዲሞቱ ሰነፎችና ደንቈሮዎች በአንድነት እንዲጠፉ ገንዘባቸውንም ለሌላዎች እንዲተ ዉ አይቷል 11በልባቸውም ቤታቸው ለዘለዓለም የሚኖር ማደሪያቸውም ለልጆች ልጅ የሚኾን ይመስላቸዋል በያገራቸው ም ስማቸው ይጠራል 12ሰው ግን ክቡር ኾኖ ሳለ አያውቅም እንደሚጠፉ እንስሳዎች መሰለ 13ይህች መንገዳቸው መሰናክላቸው ናት ከነርሱም በዃላ የሚመጡ በአፋቸው ዕሺ ይላሉ 14እንደ በጎች ወደ ሲኦል የሚኼዱ ናቸው እረኛቸውም ሞት ነው ቅኖችንም በማለዳ ይገዟቸዋል ውበታቸ ውም ከመኖሪያቸው ተለይታ በሲኦል ታረጃለች 15ነገር ግን እግዚአብሔር ይቀበለኛልና ነፍሴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል 16የሰው ባለጠግነት የቤቱም ክብር በበዛ ጊዜ አትፍራ 17በሞተ ጊዜ ከርሱ ጋራ ምንም አይወስድምና ክብሩም ከርሱ በዃላ አይወርድምና 18በሕይወቱ ሳለ ነፍሱን ባርኳልና ለሰውነቱ መልካም ብታደርግለት ያመሰግንኻል 19ኾኖም ወዳባቶቹ ትውልድ ይወርዳል ለዘለዓለም ብርሃንን አያይም 20አእምሮ የሌለው ክቡር ሰው እንደሚጠፋ እንስሳዎች መሰለ