በሁለተኛ ሰንበት ማግሥት የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር።
1እግዚአብሔር ትልቅ ነው በአምላካችን ከተማ በተቀደሰ ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው 2በሰሜን ወገን በመልካም ስፍራ የቆመ የምድር ዅሉ ደስታ የጽዮን ተራራ ነው ርሱም የትልቁ ንጉሥ ከተማ ነው 3እግዚአብሔር በአዳራሾቿ መጠጊያ ኾኖ ይታወቃል 4እንሆ ነገሥታት ተከማችተው በአንድነት መጥተዋል 5እነርሱስ አይተው ተደነቁ ደነገጡ ታወኩ 6መንቀጥቀጥ እንደ ወላድ ምጥ በዚያ ያዛቸው 7በኀይለኛ ነፋስ የተርሴስን መርከቦች ትሰብራለኽ 8እንደ ሰማን እንዲሁ አየን በሰራዊት ጌታ ከተማ በአምላካችን ከተማ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያጸና ታል 9አምላክ ሆይ በሕዝብኽ መካከል ምሕረትኽን ተቀበልን 10አምላክ ሆይ እንደ ስምኽ እንዲሁም እስከምድር ዳርቻ ድረስ ምስጋናኽ ነው ቀኝኽ ጽድቅን የተሞላ ች ናት 11አቤቱ ስለ ፍርድኽ የጽዮን ተራራ ደስ ይበለው የአይሁድም ሴት ልጆች ሐሤት ያድርጉ 12ጽዮንን ክበቧት በዙሪያዋም ተመላለሱ ግንቦቿንም ቍጠሩ 13በብርታቷ ልባችኹን አኑሩ አዳራሿን ዐስቡ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ 14ለዓለምና ለዘለዓለም ይህ አምላካችን ነው ርሱም ለዘለዓለም ይመራናል