ለመዘምራን አለቃ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
1አሕዛብ ዅላችኹ እጆቻችኹን አጨብጭቡ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ 2እግዚአብሔር ልዑል ግሩምም ነውና በምድር ዅሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና 3አሕዛብን ከእኛ በታች ወገኖችንም ከእግራችን በታች አስገዛልን 4ለርስቱ እኛን መረጠን የወደደውን የያዕቆብን ውበት 5አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ 6ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ ዘምሩ ለንጉሣችን ዘምሩ 7እግዚአብሔር ለምድር ዅሉ ንጉሥ ነውና በማስተዋል ዘምሩ 8እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ እግዚአብሔር በቅድስናው ዙፋን ይቀመጣል 9የምድር ኀይለኛዎች ለእግዚአብሔር ናቸውና የአሕዛብ አለቃዎች ወደአብርሃም አምላክ ተሰበሰቡ ርሱን ም ከፍ ከፍ አደረጉት